ታኀሳስ ፳፯(ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መንግስት፤ ታህሳስ 26- 2007 ዓመተ ምህረት ጧት እና ምሽት ላይ በርካታ ታንኮችን እና ከባድ ብረት ለበስ የጦር ተሽከርካሪዎችን ወደ ሰሜን ኢትዮጰያ አጓጉዟል።
ከየት ቦታ እንደተነሱ ያልታወቁትና ወደ ሰሜን አቅጣጫ ያመሩት ታንኮች፤ ምሽት ላይ ወልዲያ ከተማ ማረፋቸውን ነዋሪዎቹ ተናግረዋል። መንግስት ከሰሜን አካባቢ ጥቃት ሊሰነዘርብኝ ይችላል የሚል ግምገማ ማካሄዱን ኢሳት መዘገቡ ይታወሳል።