ኩባንያዎችን ለመሸጥ የተወሰነው በውጭ ምንዛሬ እጥረት ምክንያት ነው ተባለ

(ኢሳት ዲሲ– ሰኔ 5/2010)  የኢትዮጵያ መንግስት ግዙፍ ኩባንያዎችን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል ለመሸጥ የወሰነው በውጭ ምንዛሬ እጥረት ምክንያት መሆኑን ይፋ አደረገ።

የብሄራዊ ፕላን ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶክተር  ይናገር ደሴ ለፋና ተሌቪዥን ጣቢያ እንደተናገሩት በኢትዮጵያ በተፈጠረው የእዳ ጫና እና የውጭ ምንዛሬ እጥረት ምክንያት መንግስት ግዙፍ ኩባንያዎችን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል ለመሸጥ ተገዷል።