ሰኔ አስራ አራት ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:- ቢቢሲ እንደዘገበው ከታንዛኒያ ተነስተው ወደ ደቡብ አፍሪካ በጀልባ በመጓዝ ላይ የነበሩ ኢትዮጵያውያን በማላዊ ሀይቅ ላይ ሰምጠዋል።
ሟቾቹ የሶማሊያ ዜጎች መሆናቸው የተገለጠ ቢሆንም፣ የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮምሽነር ሰራተኞች አካባቢውን ከጎበኙ በሁዋላ እንዳረጋገጡት በርግጥም ስደተኞች የሶማሊያ ሳይሆኑ የኢትዮጵያ ዜጎች ናቸው።
መርከቧ ከአቅም በላይ በመጫኗ ሳትሰምጥ እንዳልቀረች የቢቢሲ ዘገባ ያመለክታል። እስካሁን ድረስ የ47 ሰዎች አስከሬን የተገኘ ሲሆን፣ የሌሎች ተጓዦችን እጣ ፋንታ ለማወቅ ፍለጋው ቀጥሎአል።
የመለስ መንግስት 11 በመቶ የኢኮኖሚ እድገት አገኘሁ ቢልም አገራቸውን ጥለው የሚሰደዱ፣ በመንገዶች ላይ የውሀ ሽታ ሆነው የሚቀሩ ዜጎች በየጊዜው እየጨመረ ነው።
ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.
ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide