ከወልቃይት ተፈናቅለው ጎንደር ከተማ የሚገኙ 160 ወጣቶች አፋጣኝ መፍትሄ እንደሚያስፈልጋቸው የከተማዋ ነዋሪዎች ገልጹ

ከወልቃይት ተፈናቅለው ጎንደር ከተማ የሚገኙ 160 ወጣቶች አፋጣኝ መፍትሄ እንደሚያስፈልጋቸው የከተማዋ ነዋሪዎች ገልጹ
( ኢሳት ዜና ጥቅምት 09 ቀን 2011 ዓ/ም ) የጎንደር ከተማ ሰላምና ልማት ሸንጎ ህዝብ ገንኙነት ሃላፊ አቶ መንገሻ ዘውዴ እንደገለጹት እድሜያቸው ከ14 -30 የሚሆኑ ወጣቶች በአማራነታቸው በአካባቢያቸው መብታቸው ተከብሮ ለመኖር ባለመቻላቸው ወደ ጎንደር ለመሰደድ ተገደዋል። የከተማ ነዋሪዎች ለተፈናቃዮች የምግብ አቅርቦት እያደረገላቸው ቢሆንም፣ ድጋፉ በዚህ መልኩ ላይቀጥል ስለሚችል የሚመለከታቸው ሁሉ መፍትሄ እንዲፈልጉላቸው አቶ መንገሻ ጠይቀዋል። ተሰደው ጎንደር ከሚገኙት የወልቃይት ተወላጆች መካከል አንዱ የሆነው ኮቢ ጌታቸው፣ አማራ በመሆናቸው በሚደርስባቸው ችግር ምክንያት አካባቢያቸውን ለቀው ወደ ጎንደር ከተማ ለመምጣት መገደዳቸውን ገልጿል
ወጣት ኮቢ ወደ መጡበት ቦታ ተመልሰው ቢሄዱ ሊደርስባቸው የሚችለውን ችግር በመዘርዝር የአማራ ክልል እንዲረከባቸው ጥያቄ አቅርቧል። የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ የወልቃይት ጠገዴ፣ የራያና የሌሎችም ብሄረሰቦች መብቶች እንዲከበሩ፣ ቀደም ሲል የነበረው አከላለል የህዝቦችን ፍላጎት መሰረት ባለዳረገ መልኩ የተፈጸመ ስለነበር እንደገና እንዲታይ ለማድረግ እንዲሚታገል መገልጹ ይታወሳል።