የላሊበላን ጥንታዊ ገዳማት ከተደቀነባቸው አደጋ ለመታደግ መንግስት ፈጣን እና ከፍተኛ ዘመቻ እንደሚያካሂድ አስታወቀ፡፡

የላሊበላን ጥንታዊ ገዳማት ከተደቀነባቸው አደጋ ለመታደግ መንግስት ፈጣን እና ከፍተኛ ዘመቻ እንደሚያካሂድ አስታወቀ፡፡
( ኢሳት ዜና ጥቅምት 12 ቀን 2011 ዓ/ም )የላሊበላ ገዳማት አስተዳዳሪና የከተማዉ ከንቲባ የሚገኙበት የልዑካን ቡድን ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር ላሊበላ በተጋረጠበት አደጋ ዙሪያ ተወያይታዋል፡፡
ከዉይይቱ በኋላ የልዑካን ቡድኑ አባላት ለመገናኛ ብዙኀን እንዳሉት ላሊበላን የመታደግ እንቅስቃሴ በያዝነው ጥቅምት ወር ይጀመራል፡፡ የልዑካን ቡድኑ አባላት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድም ላሊበላን እንዲጎበኙ ጥሪ አቅርበዋል፡፡