ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር በጥምረት መስራት አትራፊ እንዳልሆነ አንድ የማላዊ የፓርላማአባል ገለጹ::

ግንቦት ፪ ( ሁለት ) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የማላዊ ኮንግረስ ፓርቲና የአገሪቱ ፓርላማ አባል የሆኑት ወ/ሮ ጁሊያን ሉንዛጊ ዛሬ ለአገራቸው ፓርላማ እንዳሳወቁት የማላዊ አየር መንገድ ከኢትዮጵያ አቻው ጋር በጥምረት መስራቱ አትራፊአያደርገውም ብለዋል።
ጁሊያን ሉንዛጊ አያይዘውም የአገራቸው የትራንስፖርት ሚኒስቴር መስሪያ ቤት-አየር መንገዱ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር በመሥራቱ እንዴት ትርፋማ ሊሆን እንደሚችል ሪፖርትእንዲያቀርብ ጠይቀዋል። የፓርላማ አባሏ “ትርፋማ ካልሆንን ለምን አብረን እንደምንሰራ አልገባኝም” ሲሉም ተደምጠዋል።
አየር መንገዶቹ በጥምር በጀመሩት ሥራ የኢትዮጵያ አየር መንገድ 49% ከመቶ የአክሲዮን ድርሻ ሲኖረው፤ የማላዊ መንግስትና የአገሪቱ ባለሀብቶች በጥምረት 51% ከመቶ የአክሲዮን ድርሻአላቸው።
ሁለቱ አየርመንገዶች በጋራ የበረራ ፕሮግራማቸውን በመቅረጽ ሲንቀሳቀሱ መቆየታቸውን የኒያሳ ታይምስ ዘገባ ያመለክታል።