ከንቲባውን ጨምሮ በርካታ ግለሰቦች ከአዋሳ ግጭት ጋር በተያያዘ ፍርድ ቤት ቀረቡ

ከንቲባውን ጨምሮ በርካታ ግለሰቦች ከአዋሳ ግጭት ጋር በተያያዘ ፍርድ ቤት ቀረቡ
( ኢሳት ዜና ነሐሴ 25 ቀን 2010 ዓ/ም ) የሃዋሳ ከተማ ከንቲባ አቶ ቴዎድሮስ ገቢባ እና ሌሎችም ከ100 ያላነሱ ሰዎች በሲዳማና በወላይታ መካከል ግጭት እንዲፈጠር በማድረግ ለበርካታ ዜጎች ሞትና መፈናቀል ተጠያቄዎች ተደርገዋል። የተከሳሾች ጉዳይ የሚታየው በሃዋሳ ከተማ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ሲሆን ፣ ከሳሽ ደግሞ የፌደራል አቃቢ ህግ ነው። የዞኑ የአስተዳዳሪ የሆኑት አቶ አክሊሉ አዱላ እና የማረሚያ ቤት ሃላፊውም እንዲሁ የክስ ፋይል ተከፍቶባቸዋል።
ከጨምበለላ የሲዳማ አመታዊ በአል ጋር በተያያዘ ባለስልጣናት እንዳስነሱት በሚነገረው ግጭት የበርካታ ዜጎች ህይወት በአሰቃቂ ሁኔታ ማለፉ ይታወቃል።