ከትናን በስቲያ ሰኞ ታህሳስ 27 ቀን 2007 ዓመተ ምህረት በአዲስ አበባ ወሎ ሰፈር የሚገኙ የውስጥ መንገዶች  በግድግዳ ላይ ጽሁፎችና መፈክር በተጻፈባቸው ወረቀቶች አሸብርቀው ማደራቸውን ፍትህ ራዲዮ ዘገበ።

ታኀሳስ ፳፱(ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ራዲዮው  ምንጮቹን ጠቅሶ እንደዘገበው፤ የውሎ ሰፈር የውስጥ መንገዶች ግድግዳ ላይ የተጻፉት መፈክሮች-ህዝበ-ሙስሊሙ መብቱን ለማስከበር ያነሳቸውን ያቄዎች የሚያሰተጋቡና  መብታቸውን በመጠየቃቸው የታሰሩት የሙስሊም  መሪዎች እንዲፈቱ የሚጠይቁ ናቸው።

ከተለጠፉት መፈክሮች መካከል፦”አዐባሪዎች አይደለንም፣ የታሰሩት ሙስሊሞች ይፈቱ!ኮሚቴው ይፈታ!የሂጃብ ገፈፋው ይቁም! ትግሉ ይቀጥላል! እና ፍትህ ናፈቀን!”የሚሉት ይገኙበታል።

በግድግዳ ላይ ከተጻፉትና ከተለጠፉት ባሻገር ሙስሊሞች መብታቸውን ለማስከበር ያነሷቸውን ጥያቄዎች የሚያስተጋቡ በርካታ ወረቀቶችም መበተናቸው ታውቋል።