ከቫት ጋር በተያያዘ በኮምቦልቻና በደሴ ከ15 በላይ ነጋዴዎች ታሰሩ

ሚያዚያ ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-የኢሳት የደሴ ዘጋቢ እንደገለጸው በከተማዋ ባለፈው አንድ ሳምንት ብቻ 11 ነጋዴዎች ከቫት ጋር በተያያዘ የታሰሩ ሲሆን፣ በኮምቦልቻም ሶስት ነጋዴዎች ከትናንት በስቲያ ተይዘው ታስረዋል።
ነጋዴዎቹ ቫት አልከፈላችሁም ተብለው መያዛቸውን የወረዳው ባለስልጣን መግለጻቸውን የጠቀሰው ዘጋቢያችን፣ ነጋዴዎቹ በአሁኑ ጊዜ በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ባለስልጣናቱ ከመናገር ተቆጥበዋል።