እጅግ ሰፊ ክልል የሚሸፍነው የሊማሊሞ ደን በቃጠሎ ወደመ

ሚያዚያ ፴ (ሰላሳ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም  

ኢሳት ዜና:-በሰሜን ኢትዮጵያ ከውድመት ከተረፉት ጥቂት የደን ክልሎች  መካከል በሊማሊሞ አካባቢ የሚገኘው ጥቅጥቅ ደን በእሳት መጋየቱን የኢሳት ምንጮች አስታወቁ። እሳቱ የተነሳው ከአምስት ቀን በፊት ሲሆን እስካ ዛሬ ድረስ አለመጥፋቱን ከ10 ሺ ሄክታር በላይ የሚሸፍን ደንም ሙሉ ሙሉ ማውደሙን የአካባቢው ሰዎች ይናገራሉ።  እሳቱ አንድን አካባቢ ለማራቆት ሆን ተብሎ በመንግስት ሀይሎች የተለኮሰ  ነው  በማለት ቁጣቸውን የሚገልጡት የሰሜን ጎንደር ነዋሪዎች፣ ከዚህ በፊት በዳባትና ደባርቅ አካባቢ ለዘመናት ተጠብቀው የኖሩትን የደን ክልሎች በማቃጠል፣ አገር በቀል ዛፎችን በመቁረጥ ለማራቆት የተወሰደውን እርምጃ በአስረጅነት አቅርበዋል።

ቃጠሎው የደረሰው ንግስት መናፈሻ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ሲሆን፣ መንግስት ስለ ደረሰው ቃጠሎ ምንም አይነት መግለጫ አልሰጠም። በሊማሊሞ ደን ውስጥ ብርቅየ አእዋፋትና አገር በቀል ዛፎች ይገኙበት ነበር።

በኢትዮጵያ ውስጥ ጥንታዊ ቅርሶች እና ደኖችን የማውደም እንቅስቃሴ ኢትዮጵያውያንን በእጅጉ እያሳሳበ ይገኛል።

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide