ታህሳስ ፳፰( ሃያ ስምንት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ካለፉት ሶስት ቀናት ጀምሮ የስራ ማቆም አድማ እና የተቃውሞ ሰልፍ በማድረግ ላይ የሚገኙት በአስር ሺዎች የሚቆጠሩት አፍሪካውያን የእስራኤል መንግስት ያወጣውን አዲስ ህግ እንዲቀይር፣ የታሰሩት እስረኞች እንዲፈቱ እንዲሁም የስደተኞች ጉዳይ በጅምላ ከሚታይ ይልቅ በግለሰብ ደረጃ ታይቶ ውሳኔ እንዲሰጥበት የሚሉት እንደሚገኙበት በሰልፉ ላይ ተገኝቶ የነበረው አቶ አቦየ አስምረው ለኢሳት ገልጸዋል።
“በሰላማዊ ሰልፍ ውጤት ሊመጣ ይችላል ተብሎ ይጠበቃል?” ተብሎ የተጠየቀው አቶ አቦየ፣ ተቃውሞው በዚህ ከቀጠለ ምናልባትም መፍትሄ ሊመጣ ይችላል ብሎአል። ቁጥራቸው አነስተኛ ቢሆንም ኢትዮጵያውያንም በሰልፉ ላይ ተገኝተዋል
በሰልፉ ላይ ከተገኙት አብዛኞቹ የኤርትራና የሱዳን ስደተኞች መሆናቸው ተገልጿል።