ህዳር 16 ቀን 2004 ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ አንድ የ ኢትዮጵያ ባለስልጣን ለሮይተርስ እንደገለጹት፤በጣም አነስተኛ ቁጥር ያለው የኢትዮጵያ ጦር ወደ ሶማሊያ ግዛት ገብቷል።
የደቡባዊ ሶማሊያን አብዛኛውን ክፍል ከተቆጣጠሩት የአልሸባብ ሚሊሻዎች ጋር እየተዋጉ የሚገኙትን የኬንያንና የሶማሊያን የሽግግር መንግስት ሰራዊት ለማገዝ ኢትዮጵያ ተጨማሪ ጦር እንደምትልክም፤ እኚሁ ባለስልጣን ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ ቀደም ሲል ጦሯ ወደ ሶማሊያ ግዛት እንዳልገባ ስታስተባብል መቆየቷ ይታወሳል።
እኚሁ የኢትዮጵያ ባለስልጣን፦“አክራሪዎቹ የፕሮፓጋንዳ ጠቀሚያ እንዳያደርጉት- በጣም አጭርና ውሱን ለሆነ ጊዜ ነው ጦራችንን የምንልከው”በማለት ለሮይተርስ ዘጋቢ ነግረውታል።
ባለስልጣኑ የጦሩ ቆይታ አጭር እንደሚሆን ከመንገር ለፈ፤ ለመላክ የታሰበው አጠቃላይ የሠራዊት ብዛት ምን ያህል እንደሆነ ከመግለጽ ተቆጥበዋል።
ወደ ማዕከላዊና ደቡብ ሶማሊያ በመግባት ላለፉት ምንታት በአልሸባብ ላይ ጥቃት እየፈፀመ የሚገኘው የኬንያ ሠራዊት፤በከባድ ናብና በአክራሪዎቹ የጉሬላ ታክቲክ ችግር ውስጥ መግባቱን ሮይተርስ አመልክቷል።
ይሁንና የኢትዮጵያ ጦር ወደ ሶማሊያ መግባቱ ለአልሸባብ ሮፓጋንዳ ጠቀሜታ እንደሚውልና አክራሪውን ሀይል ይበልጥ እንደሚያጠናክረው፤ የአፍሪቃን ቀንድ ፖለቲካዊ ትኩሳት በቅርበት እየተከታተሉ
ያሉ ወገኖች ስጋታቸውን እየገለፁ ነው።
እነዚህ ወገኖች ፦ “አልሸባብን ያጠናከረው፤ እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር በ2009 ዓ.ም የኢትዮጵያ ጦር የውክልና ጦርነት ለማካሄድ ወደ ሶማሊያ ዘልቆ መግባቱ ነው” ማለት በአካባቢው እየተባባሰ ለመጣው ችግር የኢትዮጵያን መንግስት ተጠያቂ ሲያደርጉ ይደመጣሉ።
በአሜሪካ የስቴት ዲፓርትመንት የ አፍሪካ ጉዳዮች ዳት ዋና ፀሀፊ ጆኒ ካርሰን የኢትዮጵያ ጦር ወደ ሶማሊያ እንዳይገባ ሰሞኑን ማስጠንቀቃቸው ይታወሳል።