በጋምቢያ ዋና ከተማ ባንጁል በማካሄድ ላይ ባለው 56ኛው አፍሪካ የሰብአዊ መብት ኮሚሽንና ህዝቦች መብቶች መደበኛ ጉባኤ ላይ ፣ አሪድ ላንድስ ኢንስቲቲዩት የተባለው ተቋም ባቀረበው ጽሁፍ ፣ ነጻነትን በማፈን የአለም ሻምፒዮን ከሆኑ አገራት መካከል ኢትዮጵያ አንዳ መሆኗን ገልጿል።
በኢትዮጵያ የሚባለውና የሚደረገው የተለያየ ነው የሚለው ድርጅቱ ፣ የአገሪቱ ህዝብ አማራጭ የመገናኛ ብዙሃንን እንዳያገኝ መታፈኑን ገልጿል። በአገሪቱ አስገድዶ መድፈር ወንጀል እየተስፋፋ መምጣቱን እንዲህ አይነት ድርጊቶችን ለማስቀረት ትምህርት የሚሰጡ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እንዲዘጉ መደረጉንም ገልጿል።
ገዢው ፓርቲ እንዳቀረበው ሪፖርት ሳይሆን ኢትዮጵያ ውስጥ የኦኮኖሚ እድገት ቢኖር ኖሮ ይህን ዜጎች በእየለቱ እየተሰደዱ በሳሃራ በራሃ፣ በሲናይ በረሃና በደቡብ አፍሪካና በሌሎችም ቦታዎች ያየናቸው ግፎች አይደርሱባቸውም ነበር ሲል ተቋሙ ገልጿል።
ኢትዮጵያ በጨለማ ዘምን ውስጥ ትገኛለች የሚለው አሪድ ላንድስ፣ ወጣቱም ተስፋው ጨልሞበት እንደሚገኝ ገልጿል።