ኢትዮጵያውያን ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ያላቸውን ድጋፍ ገለጹ

(ኢሳት ዲሲ–ሰኔ 27/2010) በአውስትራሊያ የተለያዩ ግዛቶች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የለውጥ ጉዞ ያላቸውን ድጋፍ ገለጹ።

ሰልፈኞቹ ሒደቱን ለመቀልበስ የሚንቀሳቀሱ ወገኖችንም አውግዘዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለም በጄኔቫም ጠቅላይ ሚኒስትሩ የጀመሯቸውን ለውጦች የሚደግፍ ደማቅ ሰልፍ መካሄዱም ታውቋል