ጥቅምት ፰(ስምንት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም
ኢሳት ዜና :-የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ኢትዮጵያዊውን የእርሻ ሳይንቲስት አዲስ ለተቋቋመ የሳይንቲስቶች አማካሪ ቦርድ አባልነት መረጠው፡፡
ሳይንቲስቱ ፕሮፌሰር ገቢሳ ኢጀታ 26 አባላትን ላካተተው የተባበሩት መንግስታት የሳይንቲስቶች አማካሪ ቦርድ ሲመርጥ ብቸኛ የእርሻ ሳይንቲስት እንደሆነ ኢሶሼትድ ፕሬስ ዘግቧል፡፡
አዲሱ የተባበሩት መንግስታት የሳይንቲስቶች አማካሪ ቦርድ በአለም አቀፍ በተለያዩ ዘርፍ የታወቁ ሳይንስቶችን በአባልነት ይዞ ይገኛል፡፡
አዲሱ ቦርድ በሳይንስና ቴክኖሎጂ እንዲሁም በዘላቂ ልማት ፈጠራ ዙሪያ ለተባበሩት መንግስታት ዋና ፀሀፊ ባንኪሙንና ለትላልቅ ድርጅቶች ምክርን እንዲሰጥ ታስቦ ነው የተቋቋመው፡፡
ፕሮፌሰር ገቢሳ ከአራት ዓመት በፊት ድርቅንና በሽታን የሚቋቋም የማሽላ ዝርያ በማግኘታቸው በአለም ምግብ ድርጅት ሽልማት ማግኘታቸው የሚታወስ ነው፡፡