ሐምሌ ፳፮ (ሀያ ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:- “ካናቢስ”የተሰኘ አደንዛዥ ዕፅ ወደ ለንደን ለማስገባት ስትሞክር የተያዘች አንዲት ኢትዮጵያዊት ዲፕሎማት የ33 ወር እስራት ተፈረደባት።
እንደ አሶሲየትድ ፕሬስ ዘገባ፤በዋሽንግተን የኢትዮጵያኤምባሲ ውስጥ የምትሠራው አመለወርቅ ወንድማገኝ የተባለች ዲፕሎማት፤ የዲፕሎማቲክ ከለላዋን በመጠቀም 56 ኪሎ ግራም የሚመዝንካናቢስ- በሄትሮን አውሮፕላን ማረፊያ በኩል ወደ ለንደን ለማስገባትስትሞክር ነው የተያዘችው።
ጉዳዩን ሲከታተለው የነበረውና በምዕራብ ለንደን የሚገኘው የአይስወርዝ ክራውን ፍርድ ቤትም ተከሳሿ ዲፕሎማት በ ዕጽማዘዋወር የቀረበባትን ክስ አምና በመቀበሏ በ33 ወራት እስራት እንድትቀጣ ውሳኔ አሳልፏል።
የ36 አመቷ አመለወርቅ ከአዲስ አበባ ከመነሳቷ በፊት አንድ ሰው 3 ሻንጣዎችን አድርሽልኝ ብሎ እንደሰጣት ተናግራለች። በሻንጣዎች ውስጥ ያለው ስጋና ቅመማቅመም መስሎአት እንደነበርም ገልጻለች።
___________________________________________________________________________________________________________________________________________________
ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.
ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide