ጳግሜ ፭(አምስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢሳት ለኢትዮጵያውያን አዲስ አመት የመኪና የቶምቦላ ትኬት ማዘጋጀቱ ይታወቃል። ይሁን እንጅ በተለያዩ አገራት የሚገኙ የሽያጭ ወኪሎቻችን፣ በርካታ ኢትዮጵያን የሽያጭ ጊዜው በአንድ ወር እንዲራዘም መጠየቃቸውን ተከትሎ ሽያጩን ለመጨረሻ ጊዜ ለአንድ ወር ለማራዘም መወሰኑን የድርጅቱ የገቢ አሰባሳቢ ግበረሀይል ገልጿል። ተቋሙ እጣውን አስቀድሞ በተያዘለት መረሀ ግብር ለማውጣት ባለመቻሉም ይቅርታ ጠይቋል።
በተለያዩ አገራት የሚገኙ የኢሳት የሽያጭ ወኪሎች፣ በእጃችው ያለውን ቀሪ ትኬት በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ አጠቃለው፣ የተሸጡና ያልተሸጡ ትኬቶችን አሀዝ በኢትዮጵያ አቆጣጠር እስከ መስከረም 29 ቀን በስልክ ወይም በኢሜል እንዲያስታስታውቁም ግብረሀይሉ ገልጿል። ለማእከል ያልደረሱ ቁጥሮች እንዳልተሸጡ ስለሚቆጠሩ በእጣው ውስጥ እንደማይካተቱም አስታውቋል።
እስካሁን ትኬቱን ያልገዙ ኢትዮጵያውያን በተሰጠው የአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ገዝተው ኢሳትን እየረዱ እድላችወን እንደሚክሩም ግብረሀይሉ በድጋሜ ጥሪ አቅርቧል።
በአገር ቤት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የእጣው አሸናፊ ከሆኑ መኪናውን በውጭ አገራት ለሚኖሩ ወኪሎቻችሁ በኩል ይሰጣል።
እጣው ጥቅምት 1 ፣ 2006 ዓም ህዝብ በቀጥታ በሚከታተለው መንግድ የሚወጣ መሆኑንም ገብረሀይሉ አስታውቋል።