መጋቢት ፳፮ (ሀያ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-በዚሁ የቃል ኪዳን ቅጽ ላይ ” በከተማዎች የሚካሄደውን የወረዳ፣ የክፍለከተማና የከተማ ምክር ቤት አባላት ምርጫ ነጻ ፣ ሰላማዊ፣ ዲሞክራሲያዊና በህዝብ ተአማኒነት ያለው እንዲሆን በማድረግ ድርጅታችን ኢህአዴግ አሸናፊ እን
ዲሆን የበኩሌን አስተዋጽኦ ማድረግ፣ የታላቁ መሪያችንን ጓድ መለስ ዜናዊ ሌጋሲ ለማስቀጠልና ራእዩን ከግብ ለማድረስ የገባሁትን ቃል ተግባራዊ ማድረግ” የሚል ሀረግ ተጽፎ የሚገኝ ሲሆን፣ ” በምሰራበት መ/ቤት የምርጫ ካርድ ያወጡ 5 ሰዎችን በ1 ለ5 አደረጃጃት ኔትወርክ በመያዝ ኢህአዴግን እንደሚርጡ እንቀሳቀሳለሁ” የሚል ቃል ኪዳንም ታክሎበታል።
በዚሁ ቅጽ ላይ ” በኔትወርክ ከያዝኳቸው ሰራተኞችና ነዋሪዎች ውስጥ ቢያንስ አንድ ሰው ወደ አባልነት በማምጣት ህገደንብና ፕሮግራም ተወያይቶ እንዲደራጅ በማድረግ ድርጅቱን አጠናክራለሁ፣ የምርጫ ቅስቀሳ ለማካሄድ በኔትወርክ የያዝኳቸው የመ/ቤት ሰዎች በቀን ለዚህን ሰአት በማግኘት ድጋፍ አደርጋለሁ፣ ” የሚሉና ሌሎችም ቃል ኪዳኖች ሰፍረዋል። ኢህአዴግ በመንግስት መስሪያቤቶች የዘረጋው የአንድ ለአምስት አደረጃጀት የመንግስት ስራን ለማቀላጠፍ ተብሎ የተቀየሰ እንጅ ፖለቲካዊ አላማ እንደሌለው በተደጋጋሚ ሲገልጽ መቆየቱ ይታወቃል። ይህ መረጃ ኢህአዴግ እስከዛሬ ሲሰጠው የነበረውን ማስተባበያ ውድቅ የሚያደርግ ነው።ይህ በእንዲህ እንዳለ ግንባሩ ዛሬ በአዲስ አበባ ንብን ምረጡ እያለ ሲቀሰቅስና ወረቀት ሲበትን ውሎአል።
ኢህአዴግ የሚያደርገውን የብቻ ሩጫ የሚቃወሙ 33 ፖለቲካ ድርጅቶች በመኢአድ ፣ በአንድነት፣ በሰማያዊና በመድረክ አዳራሾች በሳምንቱ መጨረሻ ህዝቡን ለውይይት መጥራታቸውን መዘገባችን ይታወሳል።