ሐምሌ ፲፮(አስራ ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅርቡ የደህንነት አባላት በጠ/ሚኒስትሩ ጽ/ቤት ያደረጉትን ስብሰባ ተከትሎ፣ ኢህአዴግ ከፍተኛ ቁጥር ያለውን የሰራዊቱን አባላትና ከባድ
መሳሪያዎችን በምሽት ወደ ሽሬ፣ ተከዜ፣ ወልቃይት፣ መተማ፣ አርማጭሆ በመሳሰሉት የሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል እያጓጓዘ ነው።
ከአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ መታፈን ጋር በተያያዘ በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የታው የህዝብ ቁጣ ያስደነገጠው መንግስት፣ ማንኛውም አይነት ተቃውሞ ቢነሳ በሚል ሰራዊቱንና ደህንነቱን እያሰማራ ነው።
ከሰሜን አካባቢዎች የመጡ የደህንነት አባላት፣ ግንቦት7 ከኤርትራ መንግስት ጋር በመተባበር ለአርሶ አደሩ የጦር መሳሪያ በማደል እስከ መሃል አገር ሊገባ ይችላል የሚል አስተያየት መስጠታቸውን
ተከትሎ ፣ ግንባሩ በድንበር አካባቢዎች ላሰማራቸው የድርጅቱ አባላት ባለሀብቶች ዘመናዊ ስልኮችን በማደል የስለላ ስራ እንዲሰሩ እንዳሰማራቸው ታውቋል።
ከተለያዩ የሰራዊቱ ክፍሎች የሚከዱ ወታደሮች ቁጥር ከመቼውም ጊዜ በበለጠ እየጨመረ በመጣበት በዚህ ወቅት፣ ኢህአዴግ የሚጠፉ ወታደሮችን ለመተካት በሚል ያወጣው የቅጥር ማስታወቂያ
የተፈለገውን ያክል የሰው ሃይል አላስገኘለትም።
የኢህአዴግ ሰራዊት በከፍተኛ የሞራል ውድቀት ላይ መሆኑን የሚናገሩት ከሰራዊቱ የሚከዱ ወታደሮች፣ በዘር ላይ የተመሰረተው አደረጃጃት፣ የምግብ አቅርቦት መበላሸት እና የሰራዊቱ የኑሮ ሁኔታ ማሽቆልቆል
ለሰራዊቱ ሞራል መውደቅ ዋና ምክንያቶች ሆነው ይጠቀሳሉ።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ኢህአዴግየመከፋፈልአደጋእንዳንዣበበት ምንጮች ገልጸዋል
የገዥውፓርቲኢህአዴግከፍተኛአመራርበተለይከአቶመለስሞትበኃላአገሪትዋንመምራትካለመቻሉጋርተያይዞ በዜጎችላይየሚወስደውየጅምላእስርናየማሳደድዘመቻበራሱአባላት
ጭምርጥያቄእያስነሳመሆኑተሰምቷል፡፡
ፓርቲዎችበሽብርተኛነትሰምፖለቲከኞችንናጋዜጠኞችላይያነጣጠረየእስርእርምጃአጠናክሮመቀጠሉበተለይ መካከለኛናዝቅተኛአመራሩአካባቢተቃውሞናጉምጉምታእየተሰማነው፡፡
ምንጮችእንደገለጹትበኢህአዴግበኩል የሚወሰደውኢ-ዴሞክራሲያዊእርምጃየህዝብአመኔታበማሳጣትየግንባሩንሕልውናችግርላይይጥላልየሚሉእና እየተወሰደያለውንጉልበትየታከለበትእርምጃ
በሚደግፉአባላትናከፍተኛካድሬዎችመካከልመቃቃርእየተፈጠረ መሆኑታውቋል፡፡
ግንባሩበተፈጥሮውከግምገማበዘለለየውስጥቅራኔንየሚፈታበትመንገድየሌለውመሆኑና ልዩነቶችከባድዋጋየሚያስከፍሉበመሆናቸውምክንያትቅሬታዎቹታምቀውእስካሁንመቆየታቸውንየገለጹት ምንጮቻችንበተለይበሠላማዊመንገድቅሬታውንከሁለትዓመትበላይለሆነጊዜእየገለጸያለውንሰፊየሙስሊም ማህበረሰብየተቃውሞድምጽለማፈንኃይልየታከለበትተደጋጋሚእርምጃ
በረመዳንየጾምወርመወሰዱሙስሊም የግንባሩንአባላትጨምሮበበርካታአባላትዘንድተቃውሞእንዲቀጣጠልምክንያትመሆኑታውቋል፡፡
ኢህአዴግበአሁኑወቅትከተቃዋሚፓርቲዎች፣ከጋዜጠኞች፣ከሲቪልማህበረሰብአባላት፣ከሙስሊሙህብረተሰብ፣ በብዛትወጣቶችንካቀፈውየኦርቶዶክስተዋህዶማህበረቅዱሳንእንዲሁም
በኑሮውድነትከሚሰቃየውሰፊህብረተሰብ እናሌሎችየኅብረተሰብክፍሎችጋርበመላተሙበመጪውምርጫበዴሞክራሲያዊ መንገድሊመረጥእንደማይችል
መገንዘቡንያስታወሱትምንጮቹበዚህየተነሳየትኛውንምዓይነትተቃውሞበኃይልለመደፍጠጥወስኖተግባራዊ በማድረግላይመሆኑንአስታውሰዋል፡፡
ይህየግንባሩእርምጃትክክልአይደለምየሚሉአባላትብቅብቅማለታቸው ግንባሩበቀጣይከባድየመሰነጣጠቅአደጋሊገጥመውእንደሚችልየመጀመሪያውምልክትመሆኑንምንጮቹጠቁመዋል፡፡