ግንቦት ፰ (ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢህአዴግ የ2007 ዓም የምርጫ ቅስቀሳውን ለአማራ ክልል የከተማ ነዋሪዎች መሬት በማከፋፈል አንድ ብሎ መጀመሩን ለማወቅ ተችሎአል።
የከተማ ነዋሪዎች 20 ሺ ብር ባንክ አስገብተውና በማህበር ተደረጅተው 1 መቶ 80 ካሬ ሜትር የቤት መስሪያ ቦታ እንደሚሰጣቸው ከተነገራቸው በሁዋላ ቀበሌዎች ይህንኑ ለማስፈጸም ምዝገባ ሲያከናውኑ ሰንብተዋል።
ገንዘቡ ያላቸውና በአብዛኛው የገዢው ፓርቲ አባላት የሆኑ ሰዎች ገንዘብ ለማስያዝ የማይችሉ ነዋሪዎችን ገንዘብ እየሰጡና እያደራጁ ሲሆን፣ ሰዎቹ ቦታውን ከተቀበሉ በሁዋላ እስከ 40 ሺ ብር ከፍለው መሬቱን መልሰው ለመውሰድ እየሰሩ መሆኑን የክልሉ ዘጋቢያችን ገልጻለች።
በንግድ ስራ ላይ መሰማራት የሚፈልጉ ወጣቶችም እንዲሁ 40 ሺ ብር አስይዘው የገበያ ማእከላትን እንደሚገነቡ የተገለጸላቸው ሲሆን፣ ገንዘቡ ያላቸው ወጣቶች ተደራጅተው ሲመዘገቡ፣ ገንዘቡ የሌላቸው ደግሞ ገንዘቡ ባላቸው ሰዎች ድጋፍ ተደራጅተው ቦታውን ከተረከቡ በሁዋላ የተወሰነ ክፍያ ተከፍሎአቸው ቦታውን ገንዘቡ ላላቸው ሰዎች መልሰው ለማስረከብ ከፍተኛ እንቅስቃሴ እየተካሄደ ነው።
ኢሳት ከአንድ ወር በፊት ይፋ ባደረገው ዘገባ ለአርሶአደሩየማዳበሪያእዳእፎይታበ2006/2007 የመኸርምርትዘመንእንደሚሰጥ፣ለከተማነዋሪዎችደግሞ በ20 ሺብርቅድመክፍያለመኖሪያቤትግንባታየሚውሉቦታዎችንእንደሚታደሉዋቸው ገልጾ ነበር።
ኢህአዴግ ባዘጋጀው የ 2007 የምርጫ የማሸነፊያስትራቴጂዎችላይ ” አርሶ አደሩንና አመራሩን የመዳበሪያ እዳ እፎይታ በ2006/2007 የመኽርምርት ዘመን እንዳ ለመንገር ፤ ተቃዋሚችን ማንኳሰስ ፣ በኢህአዴግ ላይሊነሱ የሚያስቡትን እስከ ማግለል እንዲደርስ ማሰረዳት ፣ ምርጫውን በ1 ለ 5 እንዴት ድምፅ እንደሚሰጡ ማስረዳት እና በሙከራ ማሳየት፣ያለውን የፍትህ እና የልማት ችግር ወደፊት እንደሚፈታ በተስፋ መሙላት” የሚሉትይገኙበታል።
አስተማማኝ የሆነ ድጋፍ በማይገኙባቸው በአማራእናየኦሮምያክልሎች ደግሞ “አመራሩ ኢህአዴግ ከወደቀ እስር ቤት እንደሚገባ ፤ የሚመጣው መንግስት አሁን በስልጣን ላይ ያሉትን የአመራር አካላት ቤተሰብ ምጭምር ህይወት የሚያመሳቅል መሆኑን በማስረዳት ፣’ ኢህአዴግ ወይም ሞት’ ብሎ በመነሳት ሊያሰፈፅም ይገባዋል ” የሚል ቃል በሰነዱ ላይ መስፈሩን ኢሳት መዘገቡ ይታወሳል።