ኢህአዴግ ህዳጣን ወይም አናሳ እያለ በሚጠራቸው ክልሎች የተፈፀሙ በደሎች አስከፊ መሆናቸውን የፌድራል ጉዳዩች እና የአርብቶ አደር ሚንስቴር ገለፀ፡፡
( ኢሳት ዜና ሃምሌ 11 ቀን 2010 ዓ/ም )የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በኢትዮ-ሶማሌ ክልል የፍትሕ አሰጣጥ ሂደት ላይ የታዩ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ፣ ቅሬታዎች ላይ ምርመራ በማድረግ እና ችግሮቹን በመለየት በኢፌዴሪ ሕገ- መንግሥት አንቀጽ 21 የተቀመጡ መሠረታዊ የታራሚ መብቶችን የጣሱ ድርጊቶች መፈጸማቸውን አሳውቋል።
በምርመራው መሰረት ማረሚያ ቤቱ በታራሚዎች አያያዝ ክፍተት ያለበት ሲሆን፣ 15 እስረኞች በክልሉ ማረሚያ ቤቶች ራሳቸውን አጥፍተዋል፤ 64 እስረኞች የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል፤ 11 የሚሆኑ ደግሞ በማረሚያ ቤቶች አመራር ቅጣት አወሳሰድ ችግር ለሞት ተዳርገዋል፡፡