መስከረም ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-ሦስት አጥፍቶ ጠፊዎች ባለፈው ረቡዕ በሞቃዲሾ በሚገኝ ሆቴል ውስጥ በፈፀሙት የቦንብ ጥቃት አዲሱ የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሁሴን ሼክ መሀመድ ለጥቂት ተረፉ።
ጥቃቱ የተፈፀመው አዲሱ ፕሬዚዳንት ከኬንያ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ልዑካን ጋር ስብሰባ እያደረጉ በነበረበት ሰዓት ነው።
በጥቃቱ ሦስቱን አጥፍቶ ጠፊዎች እና አንድ የ አፍሪካ ህብረት ሰላም አስጠባቂ ወታደርን ጨምሮ ሰባት ሰዎች መገደላቸውን ዓለማቀፍ መገናኛ ብዙሀን ዘግበዋል።
የኬንያ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ሳም ኦንገሪ ከፕሬዚዳንት ምዋይ ኪባኪ የተላከ መልዕክት በሚያነቡበት ጊዜ ነበር ፍንዳታው የጀመረው።
ከመጀመሪያው ፍንዳታ በሁዋላ ቀጣዩ አጥፍቶ ጠፊ ስብሰባው ወደ ሚካሄድበት ወደ ጃዚራ ፓላስ ሆቴል ለመግባት ሲሞክር በ አፍሪካ ህብረት ሰላም አስጠባቂዎች መገደሉን የህብረቱ ባለስልጣናት ተናግረዋል።
___________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________
ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.
ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide