አዲሱ የመብራት፣ የውሀና ስልክ ክፍያ ስርአት ችግር እየፈጠረ ነው

የካቲት ፩፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-በ ዶ/ር ደብረጺዮን አመራር በቅርቡ ተግባራዊ የተደረገው የመብራት፣ የውሀ እና የስልክ ክፍያዎችን በአንድነት የመክፍል ሂደት በህብረተሰቡ ላይ ከፍተኛ መጉላላት እየፈጠረ ነው።

ህብረተሰቡ ክፍያዎችን ለመክፈል ረጃጅም ሰልፎችን መሰለፍና በርካታ ሰአታትን መጠበቅ ግዴታው ሆኗል

ስራውን እንዲተገብሩ የተመረጡት በሙሉ ኢህአዴግ ካድሬዎች ሲሆኑ ፣ የኢህአዴግ አባላት ያልሆኑ የየድርጅቶቹ የቀድሞ ሰራተኞች ተንሳፋፊዎች ሆነዋል።

መንግስት የህብረተሰቡን እንግልት ይቀንሳል አገልግሎትንም ያፋጥናል ብሎ የጀመረው ለሁሉ የተሰኘ የአንድ ላይ አገልግሎት በሂሳብ መቀበያዎች እጥረት በኮምፒዩተር ማነስ እና በሰለጠነ የሰው ሀይል እና አተገባበሩን ባለመቻል የተነሳ በርካታ እናቶች፣ ሽማግሌዎች ፣ ታማሚዎች እና ጎልማሶች ሙሉቀን ተሰልፈው እንዲጠብቁ ተገደዋል።

አንድ ሰራተኛ  የስራ አተገባበሩ ከሙያዊነት ይልቅ ፖለቲካዊ አላማው ይልቃል ያሉ ሲሆን ፣ በአሁኑ ጊዜ ከኢህአዴግ አባላት ውጭ ገለልተኛ እንኳን ሆኖ የመንግስት ስራ መስራትና ማገልገል የማይቻልበት ደረጃ ላይ ተደርሷል ሲሉ አክለዋል።