አንድነት ፓርቲ በአዲስ አበባ በነጻነት ቅስቀሳ ለማድርግ አልቻለም

መስከረም ፲፯(አስራ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፓርቲው ህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ዳንኤል ተፈራ ለኢሳት እንደገለጹት፣ ሊቀመንበሩን ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳን ጨምሮ በርካታ የፓርቲው አመራሮች ቅስቀሳ በማድረግ ላይ እያሉ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ተወስደው ለሰአታት ታግተው አርፍደዋል።

ምንም እንኳ የአዲስ አበባ መስተዳደር  በመጪው እሁድ ሰላማዊ ሰልፍ እንዲያደርግ ለፓርቲው ፈቃድ ቢሰጥም ፣ ፖሊስ በበኩሉ ፓርቲው ቅስቀሳ ለማድረግ ከፈለገ ከሚመለከተው አካል ልዩ ፈቃድ ማምጣት አለበት ብሎአል።

ሰላማዊ ሰልፍ ከተፈቀደልን በሁዋላ የቅስቀሳ ፈቃድ አውጡ መባሉ ግራ እንዳጋባቸውና እንዲህ አይነት    ነገር ተደርጎ እንደማይታወቅ አቶ ዳንኤል ተናግረዋል።

አንድነት ፓርቲ በፖሊስ ማስፈራሪያ  የተነሳ ቅስቀሳ ከማድረግ ወደ ሁዋላ እንደማይል አቶ ዳንኤል ተናግረዋል።