ጥር 25 ቀን 2004 ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-አንድነት ፓርቲ በመጪው እሁድ በሊዝ አዋጁ ዙሪያ የጠራው ስብሰባ በተያዘለት እቅድ መሰረት እንደሚካሄድ ዶ/ር ነጋሶ ገለጡ
የአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር የሆኑት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ለኢሳት እንደገለጡት ፓርቲያቸው ህዝቡን በአገሩ መሬት አልባ እና ንብረት አልባ የሚያደርገውን አዋጅ አጥብቀው ይቃወማሉ። 3፡55-4፡34
ባለፈው ሳምንት ሊካሄድ የነበረው ስብሰባ የአፍሪካ ህብረት ስብሰባን ምክንያት በማድረግ ሳይካሄድ እንደቀረ ዶ/ር ነጋሶ ገልጠዋል። 2፡16-2፡50
በስብሰባው ላይ ምሁራን እና የአንድነት ፓርቲ የተወሰኑ አባላትና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ይገኛሉ ሲሉ ዶክተሩ ገልጠዋል። መድረክ በበኩሉ ከህዝብ ጋር ለመወያየት ቢአቅድም በአዳራሽ እጦት ምክንያት እንዳልቻለ ግልጧል።
ይሁን እንጅ በመጪዎቹ ጥቂት ሳምንታት ከህዝቡ ጋር ሰፊ ውይይት እንደሚያድርግ ለማወቅ ተችሎአል። በአንድ ቀን ውሎ የጸደቀው የመሬት አዋጅ በመላ አገሪቱ ቁጣን እየቀሰቀሰ ነው። በርካታ ኢትዮጵያውያን አዋጁ አገር አልባ አደርገናል በማለት ሲናገሩ ይሰማል።