(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 13/2010) በቅርቡ በጡረታ የተሰናበቱት አቶ ግርማ ብሩ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የቦርድ ሊቀመንበር ሆነው ተሾሙ።
የቀድሞው የብሔራዊ ባንክ ገዢ አቶ ተክለወልድ አጥናፉም የቦርድ አባል ሆነው መሰየማቸው ተመልክቷል።
የብሔራዊ ፕላን ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ኢዮብ ተካልኝ፣ የብሔራዊ ባንክ ምክትል ገዢው አቶ በቃሉ ዘለቀም የብሔራዊ ባንኩ የቦርድ አባላት ሆነው በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ መሾማቸውን የዘገበው አዲስ ፎርቹን ነው።
የብሔራዊ ባንክ የቦርድ ሊቀመንበር ሆነው የተሰየሙት አቶ ግርማ ብሩ በቅርቡ ከመንግስት ስራ በይፋ የተሰናበቱ መሆናቸው ይታወቃል።
ኢሕአዴግን አዲስ አበባ ላይ የተቀላቀሉትና ከምክትል መከላከያ ሚኒስትርነት ጀምሮ ሕወሃትን በታማኝነት በማገልገል ስማቸው ይጠቀሳል።
አቶ ግርማ ብሩ በኢትዮጵያ ልማት ባንክ የቦርድ ሊቀመነበርነታቸውና በሚኒስትርነታቸው ዘመን ከሙስና ጋር በተያያዘ ስማቸው ጎልቶ ከሚጠቀሱ ባለስልጣናት አንዱ ናቸው።