ግንቦት ፲ (አስር) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-ዛሬ ሻንጋይ ቻይና ላይ በተደረገው የዳይመንድ ሊግ ውድድር፣ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ገንዘቤ ዲባባ በአምስት ሺህ ሜትር የሩጫ ውድድር 14፡ደቂቃ ከ45ነጥብ 92 ሰከንድ በሆነ ሠዓት በመግባት አሸናፊ ሆነች።
በዚሁ ውድድር እንደምታሸንፍ ከፍተኛ ግምት ተሰጥቷት የነበረችው የሁለት ጊዜ የኦሎምፒክ ባለድል የሆነችው ታዋቂዋ አትሌት መሰረት ደፋር 14ደ ቂቃ፡47 ነጥብ 76 ሰከንድ በሆነ ሰዓት 2ኛ ሆና ስታጠናቅቅ፣ ኬንያዊቷ ቪዎላ ኪቢዎት ደግሞ መሰረትን ተከትላ 14፤ደቂቃ 48.ነጥብ 29 ሰከንድ በሆነ ሰዓት ሶስተኛ ሆና ጨርሳለች።
በዚሁ በዓለም አቀፍ አትሌቲክስ ማሕበር አማካኝነት በሚዘጋጀው የዳይመንድ ሊግ ውድድር ላይ በ1ሺህ 500 ሜትር ውድድር ላይ የተካፈለው ኢትዮጵያዊው መኮንን ገብረ መድህን በኬንያዊው አስበል ኪፕሮፕ ለጥቂት ተቀድሞ 2ኛ ሆኖ መጨረሱዋን ቅዱስ ሀብት በላቸው ከአውስታራሊያ ዘግቧል።