አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በለንደን በሚካሄደው ኦሊምፒክ በ5 ሺ ሜትር ለመሳተፍ የሚያስቸለውን ሚኒማ ሳያሟላ ቀረ

ሰኔ ፴ (ሰላሳ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-ትናንት በፓሪስ ዲያመንድ ሊግ ላይ በ5 ሺ ሜትር የሩጫ ውድድር ላይ የተሳተፈው ቀነኒሳ በቀለ ፣ ውድድሩን በ5ኛነት በመጨረሱ በለንደን ኦሎምፒክ ላይ በዚሁ ርቀት አይሳተፍም።

ቀነኒሳ ለሽንፈቱ መንስኤ ያደረገው በእግሩ ላይ የደረሰውን ጉዳት ነው። ” የእኔ ችግር ገና አሁን ከህመም አገግሜ መምጣቴ ነው። እያሻሻልኩ ነው። በለንደን በ10 ሺ ሜትር እሮጣለሁ። በ5 ሺ ሜትር ላይ ለማለፍ ባለመቻሌ አልወዳደርም።” ብሎአል ውድድሩን በ12 ደቂቃ 55 ሰከንድ 70 ማይክሮ ሰከንድ የጨረሰው ቀነኒሳ በቀለ።

የፓሪሱን ውድድር ደጀኔ ገብረመስቀል በ12 ደቂቃ 46 ሰከንድ 81 ማይክሮ ሰከንድ በማጠናቀቅ አሸንፏል።

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide