ጥቅምት ፳፯ (ሀያ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-የ ኢትዮጵያ መንግስት የሰብአዊ መብታቸው እንዲከበር በመጠየቃቸው አ ፍሶ ያ ሰራቸውን ኢትዮጵያውያን በ አስቸክዋይ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈታ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ለመንግስት ጥሪ አቀረበ ።
መንግስት በ አሸባሪነትና የተለያዩ የወንጀል ምክንያት እየፈጠረ ያሰራቸው ሰዎች ያደረጉት ነገር ወይም የጠየቁት ጥያቄ እራሱ ባወጣው በሀገሪቱ ህገመንግስትና በ አለም አቀፍ ህግ ተቀባይነት ያለውና ህጋዊ በመሆኑ ሊታሰሩም ሊከሰሱም አይገባም ብሎአል አምነስቲ ኢንተርናሽናል።
የመንግስት ባለስልጣናት ሙስሊሙ ማህበረሰብ ባነሳው ጥያቄ ዙሪያ ለመወያየትና በሰላም ለመፍታት ያደረገው ሙከራ አለመኖሩን ያመለከተው ያምነስቲ ኢንተርናሽናል ሪፖረት ይህም የ ኢትዮጵያ መንግስት ህዝቦች ለሚያነሱት ጥያቄ ሁሉ የሚሰጠው ምላሽ የሀይል እርምጃ መሆኑን ያረጋገጠ ነው ብሎል::በዚህ መሰረት ከሀምሌ ወር ጀምሮ ተቃውሞው በአዲስ አበባ በአንዋርና በአወሊያ
መስኪድ በክልሎች ደግሞ በደሴ፣በሀረሪ፣በጅማና በሻሸመኔ ተጠናክሮ በቀጠለ ግዜ መንግስት በወሰደው እርምጃ ተጠያቂዎቹን ለፍርድ እንዲያቀርብና ሰብስቦ ያሰራቸውን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈታ አምንስቲ ጠይቆል::
በጥቅምት ወር በገርባ በሀምሌ ወር በአዲስ አበባ በታህሳስ ወር ደግሞ በአሳሳ አርሲ በሰላማዊ ዜጎች ላይ የተፈጸመው የግድያ ወንጀል በአስቸኮይ አለም አቀፍ ደረጃውን በጠበቀ የምርመራ ስራ እንዲጣራና ወንጀለኞቹ ለፍርድ እንዲቀርቡም አምንስቲ ለአለም ማህረሰብ ጥሪአቅርቦል::