(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 19/2011) አቶ ሔኖክ አክሊሉና ሚካኤል መላከ በአስቸኳይ እንዲፈቱ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ጥሪ አቀረበ።
የአዲስ አበባ ከተማ እንደሌሎች ክልሎች ሁሉ ሙሉ መብት እንዲሰጣት በመንቀሳቀሳቸው መታሰራቸውን የገለጸው አለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ተሟጋች አምነስቲ ኢንተርናሽናል ከፍልስጤም ቆንስላ ጽሕፈት ቤት ስልጠና ወስደዋል የሚል ክስም እንደቀረበባቸው አመልክቷል።
ከትላንት በስቲያ አዲስ አበባ ላይ ተይዘው ትላንት ፍርድ ቤት የቀረቡት ጠበቃ ሔኖክ አክሊሉና አቶ ሚካኤል መላከ በአስቸኳይና ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲለቀቁ የጠየቀው አለምአቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች አምነስቲ ኢንተርናሽናል የመብት ጥያቄ በማንሳታቸው ሊታሰሩ አይገባም ብሏል።
መንግስት የፖለቲካ ምህዳሩን እያሰፋ መሔዱን እንዲቀጥልም ጥሪውን አቅርቧል።