አሜሪካ እና አውሮፓ በሩስያ ላይ ተጨማሪ ማእቀብ ጣሉ

ሚያዚያ ፳፩ (ሃያአንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሩስያ በዩክሬን የሚታየውን ችግር ለማስቆም አልቻለችም በሚል አሜሪካና የአውሮፓ ህብረት በሩስያ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ተቋማትና ለፕሬዚዳንት ፑቲን ቅርበት አላቸው በሚሏቸው ባለስልጣናት ላይ ማእቀብ ጥለዋል።

ሩሲያ ድርጊቱን አጥብቃ ተቃውማለች። በዩክሬን ምስራቃዊ ክፍል የተነሳው አመጽ አሁንም እንደቀጠለ ነው። ብዙዎች ህዝበ ውሳኔ እንዲደረግ እየጠየቁ ሲሆን፣ ሩሲያ ዩክሬንን ትወር ይሆናል የሚለውን ስጋት አጠናክሮታል።