አሁን የሚታዩት ግጭቶች ለውጥ ማቆም የሚችሉ አይደሉም ሲሉ ዶ/ር አብይ አህመድ ተናገሩ

አሁን የሚታዩት ግጭቶች ለውጥ ማቆም የሚችሉ አይደሉም ሲሉ ዶ/ር አብይ አህመድ ተናገሩ
(ኢሳት ዜና ሰኔ 29 ቀን 2010 ዓ/ም) ጠ/ሚኒስትሩ በ2011 ረቂቅ በጀት ላይ ለመወያየት ፓርላማ ተገኝተው ከአባላቱ ለተነሱት ጥያቄዎች በሰጡት መልስ የተፈጠረውን ሁኔታ ለማድፍረስ እዚህም እዛም ሙከራዎች ቢኖሩም፣ የትም አይደርሱም ብለዋል። እያንዳንዱን እንቅስቃሴ መንግስት የሚያውቀውና የሚቀጫቸው ናቸው ያሉት ጠ/ሚኒስትር አብይ፣ ያሉት ባዶ ፋላጎቶች እንጅ አጠቃላይ ለውጥ ማቆም የሚችልዩ አይደሉም ብለዋል። “ፖለቲከኞች ነገር ሲሞትና ሲድን አያውቁም” የሚሉት ዶ/ር አብይ፣ እንዲህ አይነት ሙከራዎችን መንግስት ከህዝብ ጋር ሆኖ ሊያቆማቸው ይገባል ብለዋል።
ዶ/ር አብይ በውጭ አገር የሚገኙ ኢትዮጵያውያን አገራቸውን የሚደግፉበት የዲያስፖራ ፈንድ ለማቋቋም ማሰባቸውንም ተናግረዋል። እያንዳንዱ ዲያስፖራ በቀን አንድ ዶላር ከማኪያቶው ቀንሶ እንዲሰጥ ጠ/ሚኒስትሩ ጥሪ አቅርበዋል።