ጥቅምት ፳፱ (ሀያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱ 25 የፖለቲካ ፓርቲዎች 18 ጥያቄዎች የያዘ ደብዳቤ ለብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ ማስገባታቸውን አስታወቁ።
የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በቅርቡ ሊያካሂድ ባሰበውና የጊዜ ሰሌዳ ባወጣለት የወራዳና የአንዳንድ ዞኖች የሞማያ ምርጫ ነጻና ፍትሀዊ እንዲሆን እሁድ እለት ተሰብስበው ውሳኔ ያስተላለፉት 25 የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች በእለቱ ያቆቆሞቸው ሰባት አባላት ያሎቸው አስተባባሪ ኮሚቴ ከብሄራዊ ምርጫ ቦርድ 18 ጥያቄዎች የያዘ ደብዳቤ አስገብቶል።
የአስተባባሪው ኮሚቴ ሊቀመንበር አቶ አስራት ጣሴ ለኢሳት እንደገለጡት ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽፈት ቤት ይህንኑ ደብዳቤ ቢልኩም ማህተም የለውምና አንቀበልም ብለው መመለሳቸውን ገልጸዋል።
የተቀዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎቹ ነጻና ፍትሀዊ ምርጫ ማድረግ እንዲቻል ምርጫ ቦርድ ላዘጋጆቸው 18 ጥያቄዎች ላይ ተወያይቶ መልስ መስጠት አለበት ሲሉ የገለጹት አቶ አስራት ጣሴ ይህ ሳይሆን ወደ ምርጫ መግባት ትርጉም እንደሌለው አመልክተዋልም።
ባለፈው እሁድ 34ቱ የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ ያቀፈ ስብሰባ ለማድረግ ታቅዶ 25 አባላቱ መሰብሰባቸውን የገለጹት አቶ አስራት ጣሴ ይህ ሳይሆን ወደምርጫ መግባት ትርጉም እንደሌለው አመልክተዋል።
ባለፈው እሁድ 34ቱ የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ ያቀፈ ስብሰባ ለማድረግ ታቅሮ 25 አባላቱን መሰብሰባቸውን የገለጹት አቶ አስራት ዘጠኙ ፓርቲዎች በመንግስት ሰዎች በደረሰባቸው ማስፈራሪያ ወደስብሰባው ሳይመጡ መቅረታቸውን ገልጠዋል።
ሰባት አባላት ያሉት አስተባባሪ ኮሚቴ በነገው እለት በአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ቢሮ የ 25ቱን የፖለቲካ ፓርቲዎች አቅም የሚያንጸባርቅ ጋዜጣዊ መግለጫ እንደሚሰጡ ለማወቅ ተችሎል።