መጋቢት ፫ (ሶስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ፣ ባንኪ ሙን ደቡብ እና ሰሜን ሱዳንን እያወዛገበ በሚገኘው የአቢይ ግዛት ለሰፈረው የሰላም አስከባሪ ጦር ሜ/ጄኔራል ዮሀንስ ገብረመስቀልን ሾመዋል።
ሜ/ጀኔራል ዮሀንስ ከዚህ ቀደም የሀይሉ አዛዥ የነበሩትን ሌተናንት ጄኔራል ታደሰ ወረደን መተካታቸውን የተመድ ቃል አቀባይ ማርቲን ንስርኪይ ተናግረዋል።
አዲሱ ሹም በወር ከ10 ሺ ዶላር በላይ እንደሚከፈላቸው ቀደም ብለን መዘገባችን ይታወሳል።
ሜ/ጀ ዮሀንስ ገብረመስቀል በ 55 ሚሊዮን ብር አንድ ዘመናዊ ህንጻ ማሰራታቸውን በፎቶ ግራፍ አስደግፈን መዘገባችን ይታወሳል።