ግንቦት ፳፮(ሃያ ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከተመሰረተ 92ኛ ዓመቱን የደፈነው የብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት የጋዜጦችን ይዘት ለመቆጣጠር የሚያስችለውን የስምምነት ውል አሳታሚዎች እንዲፈርሙለት አስገዳጅ ሰርኩላር አሰራጭቷል፡
ማተሚያቤቱበማሽንእርጅናምክንያትጋዜጦችንበቀናቸውማተምየማይችልበትደረጃላይየሚገኝሲሆንበዚህምምክንያትጋዜጦችከመውጫቀናቸውከአንድእስከሶስትቀናትዘግይተውበመውጣትላይመሆናቸውንለጉዳዩቅርበትያላቸውወገኖችይገልጻሉ፡፡በዚህምምክንያትአቅምእያዳበሩየመጡጋዜጦችሳይቀርለኪሳራእየተዳረጉየመጡበትሁኔታእየተፈጠረሲሆንአቅምየሌላቸውከገበያለመውጣትእየተገደዱነው፡፡
ማተሚያቤቱባለፈውዓመትየህትመትሥራንበተመለከተየጋራየስምምነትውልይኑረንበሚልያሰራጨውረቂቅገዳቢሕግየጋዜጦችንይዘትአስቀድሞእንዲቆጣጠርዕድልየሚሰጠውናየማይስማማውንጋዜጦችአላትምምለማለትየሚያስችለውበመሆኑበአሳታሚዎችበኩልበተነሳተቃውሞሳይፈረምመቆየቱየሚታወስነው፡፡
በአሁኑወቅትይህንኑ ተቃውሞየገጠመውንውልአሳታሚዎችእንዲፈርሙለት፣ይህካልሆነጋዜጦችንማተምእንደሚያቆምበመግለጽሰሞኑንያሰራጨውደብዳቤበቅርቡበተመሰረተውየአሳታሚዎችማህበርበኩልተቃውሞገጥሞታል፡፡
አሳታሚዎቹከዚህይልቅ ማተሚያቤቱየመንግስትጋዜጦችንካተመበሃላበማሽንተበላሽቶአልስምየግልጋዜጦችበቀናቸውእንዳይወጡየሚያደርገውሃላፊነትየጎደለውአድሎአዊ አሰራርለማረምናአዳዲስማሽኖችንለማስገባትቅድሚያሰጥቶእንዲሠራበመጠየቅላይናቸው፡፡በሁለቱወገኖችበኩልያለውአለመግባባትይህዜናእስከተጠናቀረበትቀንድረስእልባትአላገኘም፡፡
90 ሚሊዮን ህዝብ በሚኖሩባት ኢትዮጵያጋዜጦችን በተሻለ ሁኔታ ለማተም የሚያስችል ብቸኛው ማተሚያ ቤት ብርሃንና ሰላም ነው።