ሰኔ ፪(ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-እንደ ቢቢሲ ሪፖርት፤በሀገሪቱ ታላቅ አውሮፐላን እሀድ እለት በተከፍተው ጥቃት አስር የጥበቃ ሰራተኞችን ጨምሮ በትኝሹ 28 ሰዎች የተገደሉ ሲሆን፤ የታሊባን አማጺዎች ለጥቃቱ ሀላፊነቱን ወስደዋል።
ጥቃቱ የተጀመረው እሁድ ማምሻው ላይ ለካርጎ ጭነት እና “ለቪ. አይ፣ፒ” በረራ በሚያገለግሉት የካራቺ ዓለማቀፍ አውሮፕላን ማረፊያው ክፍሎች ላይ ነው።
ሰኞ ማለዳ በአውሮፐላን ማረፊያው አዲስ የተኩስ ልውውጥ መሰማቱን ተከትሎ የሀገሪቱ ባለስልጣናት በሰጡት መግለጫ አውሮፕላን ማረፊያ ከአማጽያኑ ቁጥጥር ውጪ መሆኑን እና ሰኞ ከቀትር ጀምሮ መደበኛ የበረራ አገልግሎቱን እንደሚሰጥ አስታውቀዋል።
ካራቺ ፣ በተደጋጋሚ ለታሊባን ጥቃቶች የተጋለጠች ከተማ መሆኑዋን ቢቢሲ አውስቶአል።
የዓማጺያኑ ቃል አቀባይ ሻሂዱላህ ሻህዲ ፦”ጥቃቱን የፈጸምነውየፓኪስታን መንግስት በንጹሀን እና ሰላማውያን መንደሮች እየፈጸመ ላለው የቦንብ ጥቃት አጸፋ መመለስ በምንችልበት ህልውና ላይ እንደምንገኝ መል እክት ለማስተላለፍ ነው” ብለዋል።
ተንታኞች፤ አሁን የተፈጸመው ጥቃት ጠቅላይ ሚኒስትር ናዋስ ሻሪፍ ከታሊባን ጋር የሰላም ድርድር ለማድረግ እያሳዩ ባሉት ተነሳሽነት ላይ ተጽእኖ ሳይፈጥርባቸው እንደማይቀር እየተናገሩ ነው።