ህዳር ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-ይህን ግጭት ተከትሎም የግብጽ ሰራዊት ከፕሬዚዳንቱ ቤተመንግስት አካባቢ ተቃዋሚዎችንና የመገናኛ ብዙሀን አባላትን በማስወጣት ላይ ይገኛል::
ከቤተ መንግስቱ አካባቢ እንዲለቁ በተሰጣቸው የሰአት ገደብ መሰረት አብዛኖቹ ተቃዋሚዎች መልቀቃቸው ሲታወቅ የተወሰኑ የተቃዋሚ አክቲቪስቶች በዛው እንደሚገኙ የቢቢሲዘገባ አመልክቶል::
ይህ በእንዲህ እንዳለ ዋነኛው የግብጽ እስላማዊ አካል ፕሬዚዳንት ሙርሲ የሀገሪቱን አጠቃላይ ስልጣን እንዲቆጣጠሩ ያስችላቸዋል የተባለውን ህግ እንዲያነሱ ጠይቆል::
የአል አዛሪ ማእከል በበኩሉ ፕሬዚዳንት ሙርሲ ከተቃዋሚዎቻቸው ጋር ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ለውይይት እንዲቀመጡ ጠይቆል::
ፕሬዚዳንት ሙርሲ የህግ አካሉን ስልጣን ጭምር እንዲቆጣጠሩ የሚያደርግና እሳቸው የወሰኑትን ውሳኔ የትኛውም የህግ አካል እንዳይቀለብስ ያስቻላል የተባለ ህግ በኖቬምበር 22 ይፋ ማድረጋቸው ነበር የአሁኑን ተቃውሞ ያስነሳው::
ፕሬዚዳንት መሀመድ ሙርሲ ሙስሊም ብራዘር ውድን ወክለው ተቃዋሚዎችን በጠባብ ልዩነት በማሸነፍ ፕሬዚዳንት ለመሆን መብቃታቸው ይታወቃል::