መጋቢት ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከ20 በላይ ለሆኑ ኢትዮጵያውያን ሞት ምክንያት የሆነውን በጉጂ ዞን የተከሰተውን የጎሳ ግጭት ለማስቆም የኦሮሞ የአገር ሽማግሌዎች ወደ አካባቢው ተንቀሳቀስው የሁለቱን ጎሳዎች ሰዎች ካነጋገሩ በሁዋላ ላለፉት 4 ቀናት የተካሄደው ግችት ሊቆም ችሎአል።
ምንም እንኳ ግጭቱ ቢቆምም ውጥረቱ ግን አሁንም እንዳለ ነው። ለግጭቱ መነሳት ምክንያት ሆነዋል የተባሉ የአካባቢው ባለስልጣናት እስካሁን ተጠያቂዎች አለመሆናቸውን የሚናገሩት ነዋሪዎች፣ ግለሰቦቹ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እስካልተካሄደባቸው ድረስ መልሰው ግጭት ሊያስነሱ ይችላሉ ሲሉ ስጋታቸውን ገልጸዋል።