በጅቡቲ መስመር ፍተሻው ተጠናክሮ ቀጥሎአል

የካቲት ፪ ( ሁለት )ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከጅቡቲ ወደብ ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ እቃዎችን የሚያመላልሱ የከባድ ተሽከርካሪ ሹፌሮች እንደተናገሩት ካለፉት አራት ቀናት ጀምሮ በአዋሽ 7 ኬላ ላይ ከፍተኛ ፍተሻ እየተካሃደ በመሆኑ በስራቸው ላይ ችግር እየፈጠረ ነው።
በአሁኑ ሰአት መኪኖች ከ3 እስከ 5 ኪሜትሮች የሚደርስ ሰልፍ ሰርተው ለመፈተሽ ወረፋ በመጠባበቅ ላይ ሲሆኑ፣ ፍተሻው ከዚህ ቀደም ከነበረው የተጠነከረ ነው ይላሉ። የአሁኑ ፍተሻ በደፈናው ጥቆማ ተገኝቷል በሚል ምክንያት የሚካሄድ መሆኑን እንጅ ዝርዝር ምክንያቱ ለማወቅ አለመቻላቸውን ሼፌሮች ተናግረዋል።