መስከረም ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-በጅቡቲ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች የታሰሩት የአቶ መለስ ዜናዊ ሞት ይፋ በሆነበት ወቅት ደስታችሁን ገልጻችሁዋል ተብለው ነው። 20 የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን በጅቡቲ እና በኢትዮጵያውያን የደህንነት ሰዎች ታፍነው በነሀሴ ወር መጨረሻ ላይ በደወሌ በኩል አድርገው ተወስደዋል።
ከታሰሩት ወጣቶች መካከል ማሙሸት አንዳርጌ፣ ሰለሞን፣ ብዙአየሁ፣ ያሬድ በልበላ፣ አለማየሁ፣ ወንዶሰን፣ አንዳርጌ፣ ቴዎድሮስ፣ እንዲሁም ስማቸው ያለተገለጠ ሁለት ሴቶች ይገኙበታል።
ወጣቶቹ ለአንድ ወር ያክር በጅቡቲ እስር ቤት ከቆዩ በሁዋላ ነው ወደ ኢትዮጵያ የተላኩት።
የኢትዮጵያ መንግስት ከጅቡቲና ከሱዳን መንግስታት ጋር ባለው ግንኙነት፣ በተቃዋሚነት የሚጠረጥራቸውን ሁሉ እያሳደነ እንደሚወስድ ይታወቃል።
___________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________
ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.
ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide