ግንቦት ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በጀርመን-ባየርን ክልል የሚገኙ ወደ 60 የሚጠጉ ኢትዮጰያውያን ስደተኞች የረሀብ አድማ ለማድረግ የተገደዱት የኢትዮጵያ ስደተኞች ጉዳይ በጀርመን ካሉ አካባቢዎች በተለየ መልኩ በባየርን ክልል እና ፍርድ ቤት ተቀባይነት ስለማያገኝ ነው።
በከተማ መሀል ላይ በመሰባሰብ ባለፈው ረቡእ የተጀመረው የኢትዮጵያውያኑ ስደተኞች የረሀብ አድማ ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን፤ በአሁኑ ወቅት የሶሪያ፣የሊቢያ እና የኢራቅ ስደተኞችም በአድማው ከኢትዮጵርያውያኑ ጋር እየተቀላቀሉ ነው።
አድማው የ አባቢውን ህብረተስ ትኩረት ከመሳቡም ባሻገር በርካታ ጀርመናውያን የስደተኞቹን ጥያቄ በመደገፍ ፊርማቸውን እያኖሩ ነው።
አድማው በባየርንና አካባቢው ራዲዮኖችና ቴሌቪሺኖች ሰፊ ሽፋን እየተሰጠው እንደሆነም አስተባባሪዎቹ ገልጸዋል። ኢትዮጰያውያኑ ጥያቄያቸው ተቀባይነት እስኪያገኝ ድረስ በአድማው እንደሚገፉበት አስታውቀዋል።