ህዳር 20 ቀን 2004 ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-በዴንቨር ኮለራዶ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የመንግስት ባለስልጣናት ለአባይ ግድብ ማሰሪያ ቦንድ ለመሸጥና አዲሱን የዲያስፖራ ፖሊሲ ለማስተዋወቅ የጠሩት ስብሰባ ሳይሳካ ቀረ
በአምባሳደር ተበጀ በርሄ የተመራው የልኡካን ቡድን ያቀደውን ሳይፈጽም፣ በአካባቢው በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ተቃውሞ ወደ ዋሽንግተን ዲሲ እንዲመለስ መደረጉን በኮለራዶ ኢትዮጵያውያን አክቲቪስቶች የላኩት ዜና ያመለክታል።
አምባሳደሩ ስበሰባው የህዝብ ስብሰባ እንዳልሆነ በማስታወቅ በስፍራው የነበሩት ተቃዋሚዎች አካባቢውን ለቀው እንዲሄዱ ለፖሊስ ጥያቄ ቢያቀርቡም፣ ኢትዮጵያውያኑ ግን ተቃውሞአቸውን በመቀጠላቸው ስብሰባው ያለውጤት ተብትኖአል።
በስብሰባው ላይ ከ60 የማይበልጡ የመንግስት ደጋፊዎች መገኘታቸውም ታወቋል።