(ኢሳት ሐምሌ 30/2010)ተቃውሞው የክልሉ መንግስት ከመንገድ ስራ ጋር በተያያዘ በሰጠው የተሳሳተ መረጃ ነው። ይህን ተከትሎ ህዝቡ ወደ አደባባይ በመውጣት ተቃውሞውን ሲያሰማ ውሎአል። ይህንን ተከትሎ የከተማው ህዝብ በርካታ የመንግስት መስሪያ ቤቶችን አቃጥሏል።
በዛሬው ተቃውሞ የተርጫ ከተማ ከንቲባ የአቶ አንበሰ ኡርካ ንግድቤትና መኖሪያ ቤት፣ የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ አንድነት አሸናፊ መኖሪያ ቤት፣ የገቢዎችና ማዘጋጃ ቤቶች ተቃጥለዋል።
የከተማዋ ነዋሪዎች የዞኑ አስተዳዳሪና የድርጅት ጽ/ቤትን ተጠያቂ አድርገዋል።