በዳላስ የተገደሉት ሁለት ኢትዮጵያዊያን ተጠርጣሪ ገዳይ መታወቁን የዳላስ ፖሊስ አስታወቀ። ምክንያት ንቀውኛል በማለት።
ተጠርጣሪው አብይ በለጠ ግርማ የተባለ ኢትዮጵያዊ ሲሆን፤ ተጠርጣሪው ሟቾቹን የደስታ ምግብ ቤት ባለቤቶች፤ አቶ ያየህ ይራድ ለማንና ወ/ሮ ኔነሽ ደስታን በተገደሉ እለት፤ ከምግብ ቤታቸው ጀምሮ ሲከተላቸው እንደነበር ለማወቅ ተችሏል።
ሁለቱ የደስታ ምግብ ቤታ ባለቤቶች፤ ባለፈው ረቡእ እኩለ ሌሊት ላይ ከስራ ውለው ወደቤታቸው ሲመለሱ በራቸው ላይ በጥይት ተመተው መሞታቸውን በትናንትናው ዜናችን ላይ መዘገባችን ይታወቃል።