(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 10/2010) በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የተቀሰቀሰው የኢቦላ ቫይረስ ወደ ሌሎች የሃገሪቱ የገጠር ከተሞች እየተስፋፋ መሆኑ ተሰማ።
እስካሁን በቫይረሱ 45 ሰዎች መጠቃታቸው ታውቋል።የሌሎች 25 ሰዎች አሟሟትም ምናልባት ከቫይረሱ ጋር ሳይያያዝ አይቀርም በሚል አስከሬናቸው ላይ ምርመራ እየተደረገ መሆኑ ታውቋል።
እንደዘገባው ከሆነ ቫይረሱ ወደ ገጠር ከተማዋ ማባንዳካ መዛመቱ በአንድ ሰው ላይ ምልክቱ መታየቱ ተሰምቷል።
ከተማዋ አንድ ሚሊየን ያህል ሕዝብ የሚኖርባት መሆኑ ደግሞ አደጋውን የከፋ አድርጎታል።
የአለም አቀፉ የጤና ድርጅትም በጉዳዩ ላይ አስቸኳይ ስብሰባ መጥራቱ ታውቋል።
በማንኛውም ንክኪ በከፍተኛ ፍጥነት የሚተላለፈውና በጥቂት ቀናት ውስጥ ለሞት የሚያበቃው ቫይረስ እስካሁን መድሃኒት ያለተገኘለት መሆኑ ደግሞሌላው አሳሳቢ ጉዳይ ሆኗል ብሏል ዘገባው።