በደብረ ታቦር ከተማ 2 ወጣቶች በደህንነት ሀይሎች ተይዘዉ ተወሰዱ

ሰኔ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-በፋርጣ ወረዳ በመንገድ ትራንስፓርት ውስጥ የሚሰሩ ምስጋናዉ መልካም እና   በሪሁን ዉበቴ የተባሉ ወጣቶች
ከአማራ ዲሞክራሲያዊ ሀይል ንቅናቄ እና ከግንቦት 7 ጋር ግንኙነት አላችሁ በሚል መወሰዳቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች። ገልጸዋል።

በደብረታቦር ባለፈው ሳምንት 6 ወጣቶች በተመሳሳይ ምክንያት መታሰራቸው ይታወቃል።

በፈቀደ እግዚ ኮሌጅ መምህር የሆኑት ታደሰ መንግስቴ እና  ፍቃዱ ጌትነት እንዲሁም በደብረ ታቦር የ2ኛ ደረጃ መምህር የሆነው አሸናፊ በላይ ከተያዙበት ሰኔ 5 ጀምሮ  በአዲስ ዘመን እና ወረታ ደረቅ ጣቢያዎች  ፍ/ቤት ሳይቀርቡ ታስረዉ እንደሚገኙ ታውቋል።

 

መምህር  አብይ ሀይሌ ከስማዳ ሙያ ቴክኒክ ፣ የህክምና ባለሙያው ታደሰ ባየ ፣  ብርቁ አዲሱ   ፣ ሻለቃ አለምነዉ አየለ ማስረሻ ታፈረ የተባሉ ነዋሪዎች ሰኔ 5 እና 6 ታፍሰዉ አማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቀርበዉ  ሀምሌ 1 የጊዜ ቀጠሮ እንደተጠየቀባቸው ታውቋል።