ሚያዚያ ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-ተቃውሞው ምግብን ሰበብ አድርጎ እንደተፈጠረ ቢነገርም፣ የተማሪዎች ግን ከዚህ የዘለለ ነው ተብሎአል። ትናንት ከሰአት በሁዋላ የተነሳው ተቃውሞ ዛሬም ቀጥሎ የዋለ ሲሆን ተቃውሞው ከዞኑ ፖሊስ አቅም በላይ በመሆኑ የፌደራል ፖሊስ ጣልቃ ገብቷል። ተማሪዎች በፖሊሶች ላይ የሚያወርዱት ድንጋይ መምህራኑ ከግቢያቸው እንዳይወጡ አድርጓቸው እንደነበር የደረሰን መረጃ ያመለክታል። የፌደራል ፖሊስ ግቢውን ለመቆጣጠር መሳሪያዎችን መተኮሱን አድማ በታኝ ጭስ መጠቀሙን ለማወቅ ተችሎአል። እስካሁን በግጭቱ ምን ያክል ሰዎች እንደሞቱ ለማወቅ ባይቻልም በርካታ ተማሪዎች ተይዘው መታሰራቸውን ለማወቅ ተችሎአል። በተቃውሞውም በዩኒቨርስቲው ንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል። ይህን ዜና እስካጠናቀርንበት ጊዜ ድረስ ተቃውሞው እንደቀጠለ ነው።
ከአዲስ አበባ ወደ 300 ኪሜ የሚርቀው ደብረማርቆስ የምስራቅ ጎጃም ዞን ዋና ከተማ ነው።
በሌላ ዜና ደግሞ በምእራብ ጎጃም ዞን ከውሀ ጋር በተያያዘ በተነሳ ግጭት ሰዎች ተገደሉ
ከውሀ ጠለፋ ጋር በተያያዘ በይስማላ እና ሊበን በሚባሉ ሁለት የምእራብ ጎጃም አካባቢዎች የተነሳው ብጥብጥ የ 3 ሰዎችን ህይወት ሲቀጥፍ ፣ በርካቶች ደግሞ ቆስለዋል። ግጭቱ በነዋሪዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱ ሲነገር ፣ ባህርዳር ከተማ የነበረው የፌደራል ፖሊስ ወደ አካባቢው በመሄድ ግጭቱን መቆጣጠሩን ለማወቅ ተችሎአል። ፈጥኖ ደራሽ ፖሊሶችም ግጭቱን ቀስቅሰዋል ያሏቸውን ከ40 በላይ ሰዎች ይዘው አስረዋል።
___________________________________________________________________________________________________________________________________________________
ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.
ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide