በደቡብ የሶማሊያ ግዛቶች ጠንካራ ዉጊያዎች ተቀስቅሰዋል

የካቲት 13 ቀን 2004 ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-በደቡብ ሶማሊያ ቤይ እና ባኩል ክልሎች ዉስጥ በፌዴራል

የሽግግሩ መንግሰትና በኢትዮጵያ መንግስት ወታደሮች ጥምረት እንዲሁም በሌላ በኩል የአልቃይዳ አካል በሆነዉ አልሸባብ መካከል ጠንካራ ዉጊያ በመካሄድ ላይ እንዳለ ተገለፀ።

በበርዳሌ ከተማ የሚገኙ የአይን ምስክሮች ለሸበሌ ሚዲያ በስልክ እንደገለፁት የአልሸባብ ተዋጊዎች ወታደራዊ ልምምድ በማድረግና ወደ ይዞታቸዉ እየገፉ በመምጣት ላይ ያሉትን የኢትዮጵያንና የሽግግር መንግሰቱን ወታደሮች ለመግታት መከላከያቸዉን በማጠናከር ላይ ይገኛሉ።

አንድ ስማቸዉ እንደይገለፅ የፈለጉ የሽግግር መንግስቱ ወታደራዊ አዛዥ ወታደሮቻቸዉ በሶማሊያና በኢትዮጵያ ድንበር መካከል የሚገኙ ሁለት ከተሞችን ኸደር እና ዋጂድ በቅርብ እንደሚይዙ ለሸበሌ ሚዲያ መግለፃቸዉን ኦል አፍሪካን ኒዉስ አመልክቷል።

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide