በሆላንድ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የተቃውሞ ሰልፍ እያዘጋጁ ነው

የካቲት 13 ቀን 2004 ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ ኢምባሲ የቤኑሉክስ አባል አገራት በሆነት በቤልጂየምና በኔዘርላንድስ ከሚገኙ ኢትዮጵዮጵያውያን ጋር በዲያስፖራ ፖሊሲና  በአዲሱ የሊዝ አዋጅ ዙሪያ ለመወያየት የፊታችን ቅዳሜ ስብሰባ ጠርቷል።

ኢሳት ከአዘጋጆቹ እንደተረዳው በስብሰባው እለት ኢትዮጵያውያን የተቃውሞ ድምጾችን ማሰማት ብቻ ሳይሆን፣ ይህን መንግስት በመቃወም የስደተኝነት ጥያቄ ጠይቀው የመኖሪያ ፈቃድ ያገኙትን ሰዎች በፊልም በተደገፈ ማስረጃ በማቅረብ፣ ለእየአገራቱ የስደተኝነት ጽህፈት ቤቶች ለማቅረብ ከፍተኛ ዝግጅት እያደረጉ ነው።

የኢትዮጵያ መንግስት የሚልካቸው ስደተኞች፣ መንግስትን ተቃውመው የመኖሪያ ወረቀት ካገኙ በሁዋላ ተመልሰው የመንግስት ደጋፊ በመሆን ለሰብአዊ መብቶች የሚታገሉትን ሰዎች የማስፈራራት ስራ እየሰሩ ነው።

ከዚህ በፊት በሶማሊያዋ አሊ ሂርሲ ላይ የተፈጸመው አይነት ድርጊት ስብሰባውን በሚሳተፉ ኢትዮጵያውያን ላይ እንደሚደገም አስተባባሪዎች ይናገራሉ።

በሌላ በኩል የኢትዮጵያ መንግስት በቅርቡ በኔዘርላንድስ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን 200 ሺ ዩሮ መሰብሰቡን በዜና የፋ ማድረጉን ተከትሎ፣ ራሳቸውን የኮሚኒቲው ተጠሪ ነን በማለት ድጋፍ እንዲሰባሰብ ያደረጉት ግለሰቦች ለኔዘራንድስ መንግስት ታክስ መክፈል እና አለመክፈላቸውን እንዲያረጋገጡ ክስ እንደሚመሰርቱ አስተባባሪዎች ገልጠዋል።

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide