በደቡብ ክልል ቡርጂ ግጭት ተቀሰቀሰ

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 2/2011)በደቡብ ክልል ቡርጂ አካባቢ ግጭት መቀስቀሱ ተሰማ።

          በግጭቱም በሰዎችና በንብረት ላይ ጉዳትመድረሱ ነው የታወቀው።

ፋይል

          ከኦሮሚያ ክልል ጋር ይዋሰናል በተባለው በምዕራብ ጉጂ አካባቢ የተቀሰቀሰው ግጭት ይሄ ዜና እስከተጠናቀረበት ድረስ አለመብረዱን ነው ነዋሪዎቹ የሚናገሩት።

          ግጭቱ በዋናነት የቡርጂ ብሔረሰቦች ላይ ያነጣጠረ ነው ብለዋል ነዋሪዎች ።

          በደቡብ ክልል ቡርጂ አካባባቢ ግጭቱ በዋናነት መቀስቀስ የጀመረው በ2010 መስከረም ላይ እንደሆነ ይናገራሉ ነዋሪዎቹ።

          ከኦሮሚያ ክልል ጋር በሚዋሰነው በምዕራብ ጉጂ አካባቢ በሚገኘው ቡርጂ ወረዳ የተቀሰቀሰውና በቡርጂ ማህበረሰብ ላይ ያነጣጠረው ግጭት ዛሬ የተጀመረ አይደለም ይላሉ ነዋሪዎቹ።የቆየና ከ30 በላይ ለሆኑ ሰዎች ሞትና ለበርካታ ንብረቶች ውድመት ምክንያት መሆኑን በማስቀመጥ።

          ዛሬ ላይም ይሄ ግጭት ዳግም አገርሽቶ በሰዎችና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን ነው ነዋሪዎቹ የሚናገሩት።ይሄ ዜና እየተጠናቀረ ባለበት ሰአትም ግጭቱ እንደቀጠለ መሆኑን ነው የኢሳት ምንጮች የሚናገሩት ።

          በዛሬው ግጭት እስካሁን 4 ሰዎች መገደላቸውንና ከ15 በላይ ቤቶች መቃጠላቸውም ታውቋል።

          ነዋሪዎቹ እንደሚሉት ጥቃቱን እያደረሰ ያለው የኦነግ ሰራዊት ነው  

          እስካሁን በአካባቢው ለሚከሰተው ችግር ጣልቃ ገብቶ የመፍትሄ  ርምጃ የወሰደ አካል አለመኖሩንም ነው ኢሳት ካገኘው መረጃ ማወቅ የተቻለው።